open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

ካቢኔው ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በታክስ እዳ ማቅለያ እና ገቢ መሻሻያ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ አሥተላልፎአል፡፡

በዚሁ መሠረት

1997- 2007 ግብር ዘመን ውዝፍ እዳ ለነበረባቸው ግብር ከፋዮች እዳው በምህረት ቀሪ እንዲሆን

2008 - 2011 ግብር ዘመን እዳ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ቅጣትና ወለድ ተነሥቶ ፍሬ ግብር በቻ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

ካቢኔው በተጨማሪም ቤታቸው ለተቀመጡ ሠራተኞች ደሞዝ ለሚከፍሉ ድርጅቶችና ግለሠቦች እንዲሁም ለተከራዮቻቸው የኪራይ ቅናሽ ላደረጉ አከራዮች የታክስ ጫና ማቃለያ ውሣኔዎች አሥተላልፎአል፡፡

 

በከተማ አቀፍ ደረጃ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ንቅናቄ ስራ ተጀመረ፡፡መርሃግብሩን በይፋ ያስጀመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ እና የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ እንደገለጹት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ኢትዮጵያውያን ከድህነት ለመላቀቅ የምታደርገውን ትግል እውን ማድረጊያ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡የግድቡ ትርጉም ከኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ባለፈ የኢትዮጵያውያን የክብር እና የመተባበር ተምሳሌት ጭምር በመሆኑ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች ግድቡ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ ከዚህ ቀደም ያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ ጥሪያቸው አቅርበዋል፡፡